የጠዋት ህመም ብዙ ግዜ ከ4 እስከ 9 ሳምንት መካከል ባለው የእርግዝና ግዜ ይጀምራል። ብዙ ግዜ ከ7 እስከ 12 ሳምንት መካከል ባለው ይባባሳል። ለብዙ ሴቶች ከ12 እስከ 16 ሳምንት መካከል ባለው ሁኔታው እየተሻሻለና የጠዋት ህመሙ እየጠፋ ይመጣል። ከጥቂቶቹ ሴቶች መካከል በእርግዝና ወቅት ማቅለሽለሽና ማስታወክ ለብዙ ሳምንታትና ወራት ይቆይባቸዋል፤ አንዳንዶቹ ደግሞ በእርግዝናው ወቅት በሙሉ ይቋቋሙታል።
ለስጋና ዶሮ ጥላቻ ማሳደር የተለመደ ነው። እንደውም አንዳንድ ሴቶች ጠንካራ ጣእምና/ወይም ሽታ ያላቸውን አትክልቶችና መጠጦች መቋቋም አይችሉም። በእርግዝና ወቅት ማቅለሽለሽና ማስታወክ የተፈጥሮ መከላከያ ዘዴ እንደሆነና እናቶችና ያልተወለዱ ጨቅላዎቻቸውን ከጎጂ መርዞች ሊከላከልላቸው እንደሚችል ጥናቶች ይናገራሉ።
አያስቡ፦ ጽንሱ የሚያስፈልገውን ምግብ ሁሉ ከእርስዎ ያገኛል። ልጁ ላይ አደጋ ወይም አሉታዊ ተጽእኖ እንደሌለ ጥናቶች አረጋግጠዋል። ክብደት መቀነስ የፈሳሽ ማነስ ምልክት ሊሆን ይችላል፣ ስለዚህ ምንም ትንሽ ቢሆን የቻሉትን ለመብላትና ለመጠጣት መሞከሩ አስፈላጊ ነው። ክብደት ቀንሰው አሁንም ካሳሰብዎት የማህጸን ሀኪምዎን እንዲያማክሩ ይመከራል።
ስለአደጋው ማወቅዎ አስፈላጊ ነው። ፈሳሽ የማነስ አደጋ ላይ እንደሆኑ ካሰቡ የማህጸን ሀኪምዎን ያግኙ ወይም በአካባቢው ያለ ድንገተኛ ክፍል ይሂዱ።
የፈሳሽ አወሳሰድዎን ለመጨመር ፦
ደስ አይልም ግን ያን ያህል መጥፎ አይደለም። ብዙው ምራቅ በእርግዝናው ወይም በአሲድ መጨመር የተፈጠረ ሊሆን ይችላል። ለተጨመረው አሲድ መፍትሄ መፈለግ የምራቁን መጠን ሊቀንሰው ይችላል። ብዙ ምራቅ አፍዎ ውስጥ ከተጠራቀመ ይትፉትና ብዙ ግዜ በአፍ መታጠቢያ ይለቅለቁ። ብዙ ምራቅ መዋጥ የጠዋት ህመምን ሊያባብስ ይችላል።
በእርግዝና ወቅት በሰውነትዎ ውስጥ ያለው ሆርሞን ደረጃ ይጨምርና የምግብ መፈጨት ይዘገያል። በመቀጠል ምግቡ “ጨጓራዎ ውስጥ ቁጭ እንዳለ”ና ማውጣት እንዳብዎት ሊሰማዎት ይችላል። ለተሻለ የምግብ መፈጨት ህክምና አማራጮች የማህጸን ሀኪምዎን ያማክሩ።
አዎ። በእርግዝና ወቅት በማቅለሽለሽና ማስታወክ የሚሰቃዩና ምልክቶቹ በስራ ላይ ብቃታቸው ላይ ተጽእኖ እንደሚያሳድሩ የሚሰጉና የሚያስጠላቸው ብዙ ሴቶች ቤት ለመቆየት እረፍት ወይም የህመም እረፍት ይወስዳሉ።
በርግጥ አለው። ጭንቀት፣ ድብርት፣ብስጭትና መጫጫን ማቅለሽለሹን ሊያባብሱት ይችላሉ። ስለዚህ ስሜታዊነትዎንና መጫጫንዎን ሊቋቋሙ የሚችሉበትን መንገድ ማመቻቸትና መልመድ አስፈላጊ ነው።በማቅለሽለሽ & ማስታወክ እና ስሜታዊ ሁኔታ መካከል ስላለው ግንኙነት ተጨማሪ መረጃ እዚህ ጋር ይጫኑ።
አዎ። እንደ ልማድ ትንንሽ ምግብ መመገብ ይቀጥሉ እንዲሁም ሁሉም ምግብ ላይ ገንቢ ምግብ ይጨምሩ። ይህ በእርግዝናው ሙሉ በደም ውስጥ ያለውን የስኳር መጠን ለማስተካከል ይረዳዎታል። እረፍት መውሰድዎን ያረጋግጡ። ያስታውሱ፣ ሲርብዎት፣ ጨጓራዎ ለረጅም ሰአት ባዶ ሲሆን ወይም ብዙ ሲበሉ የጠዋት ህመም ተመልሶ ሊሰማ ወይም ሊባባስ ይችላል።
ይጠንቀቁ! የአሁኑ ማቅለሽለሽዎ ምንጩ ሌላ ነገር እንደሆነ ጭንቀት አለ። የማህጸን ሀኪምዎን በቶሎ ያማክሩ።