በእርግዝና ወቅት የማቅለሽለሽና ማስታወክ ሁኔታ (“የጠዋት ህመም” የሚባለው) እስከ 85% እርጉዝ ሴቶችን የሚያጋጥም የታወቀ አስቸጋሪ ሁኔታ ነው። በቀን ወይም በማታ በማንኛውም ሰአት ሊፈጠር የሚችልና ምልክቶቹ ከሴት ሴት የሚለያይ ነው። ብዙ እርጉዝ ሴቶች ለተወሰኑ ሽታዎች፣ ጣእሞች፣ እይታዎች፣ ንኪኪ ወይም ወሲባዊ ግንኙነት ጥላቻ ያዳብራሉ። እነዚህ ለውጦች አንዳንድ ጊዜ መወዛገብን ይፈጥራሉ፣የትዳር አጋርዎን ሊያስከፋ እንደውም ሊያጣላና ሊያስቀይም ይችላል።
በጠዋት ህመም የምትሰቃይ ሚስት፣ የቤተሰብ አባል ወይም ጓደኛ ካለዎት የሚከተሉትን በማድረግ ማገዝ ይችላሉ፦
- ምን እንደሚያስጠላት ማወቅና ማስወገድ።
- በእርግዝናው ሆርሞኖች ምክንያት የሚፈጠሩ ለውጦችን (ለማሳሌ የስሜት መቀያየር፣ መጫጫን፣ አለመመቸት፣ የሰውነት መቀየር) ይጠንቀቁ።
- በቂ ፈሳሽ እንድትወስድ በየ ከ1 እስከ 2 ሰዐታቱ መጠጥና መዳረሻ (ስናክ) ያስታውሷት እንደውም ያቅርቡላት።
- መዳረሻ (ስናክ) ያዘጋጁላት።
- ከማብሰልና ምግብ ከማዘጋጀት ወይም የተሰራ ምግብ ቤት ከማምጣት ያድኗት።
- የቤት ስራ፣ ልጆች መንከባከብና የመሳሰሉትን ያግዟት።
- እንድታርፍ ያስታውሷት። በእርግዝና ወቅት በተለይ የእርግዝናው መጀመሪያና መጨረሻ ላይ ሴቶች ከተለመደው በተለየ ይደክማቸዋል።
- ፍቅር፣ ሀዘኔታና እርዳታ ያሳዩ።
- ያለችበትን ሁኔታ በተሻለ የሚያስረዳውንና እርስዎ እንዲያግዟትና ነገሮችን እንዲያቀሉላት የሚረዳዎትን የዚህን ድህረ-ገጽ የተለያዩ ክፍሎች እንዲያነቡ እንመክራለን።




