በጠዋት ህመምና በአዕምሮ ችግሮች መካከል ያለው ግንኙነት

הקשר בין בחילות בוקר למצב נפשי

ምላሹ የማያጠራጥር ነው፦ የጠዋት ህመም የአዕምሮ ችግር ምልክት አይደለም!

ሰዎች የሚከተሉትን ሊነግርዎት ይችላሉ፦

  • “ሁሉም ነገር ጭንቅላትሽ ውስጥ ነው ያለው”።
  • “ለመልመድ ሞክሪ። የተለመደ ነው”።
  • “ያን ያህል አስቸጋሪ አይደለም”።
  • “የጠዋት ህመም ሰውነትሽ ልጁን ያለመቀበሉ ምልክት ነው”።
קשר נפשי ובחילות בהיריון

ከነዚህ አባባሎች አንዳቸውም እውነት አይደሉም! ሰዎች እርስዎን ለመርዳት ቢሆንም እንደዚህ ያሉት አንዳንዶቹ አስተያየቶች ወይም ድርጊቶች የጭንቀት፣ ሀዘን ወይም ስጋት ስሜት ሊያስከትልብዎት ይችላሉ። እነዚህ ስሜቶች ለእርስዎና ማህጸንዎ ውስጥ ላለው ጽንስ ጥሩ ስላልሆኑ ቦታ ላለመስጠት መፍትሄ ይፈልጉ ወይም ቢያንስ አጠገብዎ ላሉ ሰዎች እነዚህ ድርጊቶችና ወሬዎች እንደሚጎዳዎት ይጠቁሟቸው። 

በጠዋት ህመም የሚሰቃዩ ብዙ ሴቶች ስሜታቸው ላይ የሚያመጣው ተጽእኖ አዕምሯዊና አካላዊ እንደሆነ ይናገራሉ። ሌሎች ሰዎች ምን እንደሚሰማዎት ሁሌ እንደማይረዱዎትና ስቃይ የሚያስከትልብዎትን የሚሰማዎትንና ስሜትዎን እውነት አይደሉም እንደሚሉ ይገምታሉ።

ነገር ግን የሚሰማዎት ስሜቶች እውነተኛ ናቸው እንዲሁም ህይወትዎን መምራት እንዳልቻሉ፣ የቤትና/ወይም የቢሮ ውስጥ የእለት እለት ስራን አለመቻል ሊሰማዎት ይችላል። ባለቤትዎ፣ ጓደኞችዎ፣ ቤተሰብዎና ሌሎች ካልተረዱዎት ስለዚህ ጉዳይ ማወቅ እንዲችሉ ወደ ስለሚሰማዎት ምልክቶች እንዲያውቁና እንዴት ሊረድዎት እንደሚችሉ ድህረ-ገጽ ይጠቁሟቸው።

ሀላፊነትዎን መወጣት ካልቻሉና ሁኔታው ከፈቀደልዎት ትንሽ እረፍት ቢያገኙ ይመረጣል። እረፍትና እንደ ሽታ፣ ጫጫታና እንቅስቃሴ ያሉ እንቅልፍ የሚነሱ ሁኔታዎችን መቀነስ የተሻለ ስሜት ይፈጥርልዎታል። እንዲሁም ስሜትዎንና የሚሰማዎትን ሊያዋሩት የሚችሉት ሰው ለማግኘት ይሞክሩ። ለሙያዊ መረጃ የሚከታተልዎትን ሀኪም እንዲጠይቁ ይመከራል።

የጠዋት ህመም በኑሮዎ ጥራት ላይ መጥፎ ተጽእኖ ሊኖረው ይችላል። የጠዋት ህመም የሚያጋጥማቸው ብዙ ሴቶች የድብርት፣ ጭንቀት፣ መገለል፣ መበሳጨት ይሰማቸዋል እንዲሁም ጉልበት ስለማጣት ያማርራሉ። ስለስሜታቸውና ስለሚሰማቸው ሁኔታ ያዝናሉ፣ ብዙ ሴቶች የሚከተሉት ያጋጥማቸዋል፦ 

  • የወላጅነት ችሎታቸው ጫና ይፈጠርበታል።
  • ከልጆቻቸው ጋር በቂ ጊዜ ማሳለፍ አይችሉም።
  • እንደ አስቤዛ መግዛት ወይም የማህበራዊ ኑሮ ስብሰባዎች ያሉ የተለመዱ እንቅስቃሴዎች ይቋረጣሉ።
  • በነዚህ ምልክቶቻቸው ምክንያት የህመም እረፍት ወይም ከስራ ፈቃድ ይወስዳሉ። የገንዘብ ወጪው ተጽእኖም ቀላል አይደለም።

ጥሩው ዜና ብዙ ጥናቶች የጠዋት ህመም በእርግዝናው ሂደት ላይ የመከላከል ውጤት መኖሩ ነው፤ ይኸውም የጽንስ መጨናገፍና አብሮ የሚወለዱ መዛባቶችን መጠን መቀነስና ጤነኛ ልጅ የመወለድ እድሉን መጨመር ናቸው።

አጋራ:

Share on facebook
Share on twitter
Share on linkedin

רוצה ללמוד על בחילות והקאות בהריון וכיצד להתמודד איתן?

רוצה ללמוד על בחילות והקאות בהריון וכיצד להתמודד איתן?

Play Video