ሃይፐርሚስስ ግራቪዳረም (HG) ምንድን ነው?

בחילות בהריון כל היום

በህክምና ቋንቋ በጣም አደገኛ ደረጃ ያለው ማቅለሽለሽና ማስታወክ “ሀይፐርሚስስ ግራቪዳረም” ይባላል። የሀይፐርሚስስ ግራቪዳረም ትምህርትና ጥናት ማህበር ሁኔታውን “በእርግዝና ወቅት የሚፈጠር በአግባቡ የመመገብና የመጠጣት ችሎታን የሚከለክል እጅግ የበዛ ማቅለሽለሽና ማስታወክ” ብሎ አብራርቶታል። ሁኔታው ያልተለመደ የእርግዝና ውስብስብነት ነው ተብሎ ይገመታል። በዚህ ሁኔታ የሚሰቃዩ ሴቶች ከመቶኛው 0.3%-2% ነው።

የሀይፐርሚስስ ግራቪዳረም አደጋ መኖር መንስኤዎች የሚከተሉት ናቸው፦ በቀድሞ እርግዝና በሽታው ከነበረ፣ ጤናማ ያልሆነ ውፍረት፣ ብዙ ጽንስ ያለው እርግዝና፣ የመጀመሪያ እርግዝናና ማህጸን ውስጥ ያልተለመደ የህዋስ መራባት የሚያስከትል ጀስቴሽናል ትሮፎብላስቲክ የሚባል በሽታ።

የሀይፐርሚስስ ግራቪዳረም ብዙ ግዜ የሚከሰተው በመጀመሪያው የእርግዝና ክፍል ነው። የዚህ በሽታ የመጀመሪያው ምልክቶች የሚከተሉት ናቸው፦ በቀን ከ3-4 ጊዜ ማስታወክ፣ 2.5ኪሎ የሚሆን ክብደት መቀነስ፣ በማቅለሽለሹና ማስታወኩ የሚከሰት ራስ ማዞር፣ በማቅለሽለሹና ማስታወኩ ምክንያት ለመመገብና መጠጣት አለመቻል፤ ይህ ወደ ፈሳሽ ማጣት ያመራል።

በእያንዳንዱ እነዚህ ጉዳዮች በፍጥነት ህክምና እንዲያገኙ ይመከራል።

የሁኔታው ምርመራ በሀኪሙ ጥያቄዎች፣ የህክምና ታሪክ፣ አካላዊ ምርመራና አንዳንዴ ሀኪሙን በምርመራው ሂደት የሚያግዙ የላቦራቶሪ ውጤቶች መሰረት ነው።

אשה מקיאה בהיריון

የሀይፐርሚስስ ግራቪዳረም ህክምና የተለያዩ የፈውስ አማራጮችን፣ ብዙ ትንንሽ ምግቦችን መመገብ፣ ደረቅ ምግቦችን (ክራከርስ ወዘተ) መመገብና የአእምሮ እገዛን ይጨምራል። በብዙ አጋጣሚዎች ሴቲቱ የተወሳሰበ ህክምና ሆስፒታል ውስጥ ያስፈልጋታል፤ይህ በደም ስር የሚሰጥ ፈሳሾችንና ሌላም ይጨምራል።

በእርግዝና ወቅት ከጤና ሁኔታ ማሽቆልቆል እስከ ሀይፐርሚስስ ግራቪዳረም ሁኔታ ድረስ ማቅለሽለሽና ማስታወክን እንዴት መከላከል እንደሚቻል ለተጨማሪ ምክሮች እዚህ ጋር ይጫኑ። እንዲሁም በእርግዝና ወቅት ማቅለሽለሽና ማስታወክን የሚከለላከል  ስለአመጋገብና አኗኗር መረጃ እዚህ ጋር ይጫኑ።

በእርግዝና ወቅት በሀይፐርሚስስ ግራቪዳረም የሚሰቃዩ አንዳንድ ሴቶች ይህን ከፍተኛ ስቃይ በድጋሚ ለመቋቋም እንደማይችሉ ስለሚሰማቸው ሌላ እርግዝና ከማቀድ ይቆጠባሉ። በእርግዝና ወቅት የማቅለሽለሽና ማስታወክ ወይም የሀይፐርሚስስ ግራቪዳረም ታሪክ ካለዎት የማህጸን ሀኪምዎን አስቀድመው በእቅድ ደረጃ ላይ እያለ ወይም ማርገዝዎን እንዳወቁ ወዲያው ማማከሩ አስፈላጊ ነው። እንደዚህ ከሆነ ሀኪምዎ ክትትልና ሁኔታው ከመባባስ የሚገታው ህክምናዎትን የሚጨምር ምቹ እቅድ ሊያወጣ ይችላል፤ ይህን በማድረግ ሀኪምዎ የእርግዝና ጊዜዎን በሚቻለው ምርጥ መንገድ እንዲወጡት ያግዝዎታል።

አጋራ:

Share on facebook
Share on twitter
Share on linkedin

רוצה ללמוד על בחילות והקאות בהריון וכיצד להתמודד איתן?

המהפכה בטיפול בבחילות בהריון

רוצה ללמוד על בחילות והקאות בהריון וכיצד להתמודד איתן?

המהפכה בטיפול בבחילות בהריון

Play Video